
15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ተጀመረ።
15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ተጀመረ።
ታህሳስ 26 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የባህል ስፖርት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ።
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የባህል ስፖርት ጨዋታዎች ለዘመናዊ ስፖርት መነሻ በመሆናቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ እሴቶቻቸውን ጠብቀው ሊተላለፉ ይገባል ብለዋል።
15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር የገናን ጨዋታ ጨምሮ በ9 የባህል የስፖርት አይነቶች እስከ ጥር 8 በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ የገለጹት አቶ ዳዊት በውድድሩ አስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ 1ሺህ በላይ ስፖርተኞች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።
የውድድሩ ዋና አላማ የባህል ስፖርትን በከተማ ደረጃ በማስፋፋት ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ከተማ አስተዳደሩን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ ስፖርተኞችን ለመምረጥ እንደሆነ ምክትል ቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።
አዲስ አበባ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኮማንደር ታደሰ ጋዲሳ በበኩላቸው የባህል ስፖርትን በከተማ ደረጃ ለማስፋፋት የታዳጊ የስልጠና ፕሮጀክቶች በትምህርት ቤቶች እንደተከፈቱ አውስተው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እየተካነወነ የሚገኘው ታዳጊዎችን ባህል ስፖርት ስልጠና የመስጠት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ባህል ስፓርቶች ረዥም ዘመን ያስቆጠሩ የማንነት መገለጫ ናቸው ያሉት የውድድሩ እና ፌስቲቫሉ አዘጋጅ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዷለም አሰፋ ባህላዊ ስፖርቶች መልካም እሴቶች በማጉላት ወንድማማችነት እህትማማችነት ለማጎልበት ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በውድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም የትግል ውድድር በሁለቱም ፃታ ተካሂዷል።
15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር ፌስቲቫል በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተለያዩ ውድድሮች ቀጥሎ እንደሚውል ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.