
የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ፌስቲቫልና ትርኢት ተካሄደ
የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ፌስቲቫልና ትርኢት ተካሄደ
ታህሳስ 27 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን እና ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ፌስቲቫልና ትርኢት አካሄደ።
በቦሌ ገርጂ ትምህርት ቤት በተካሄደው የስፖርት ፌስቲቫል እና ትርኢት ከአስራንዱም ክፍለ ከተሞች የመጡ የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ተሳትፈውበታል።
በፌስቲቫሉም የተለያዩ የስፖርት ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርትን ለማስፋፋት እንደነዚህ አይነት ፕሮግራሞች ሚናቸው የጎላ እንደሆነ በፕሮግራሙ ላይ ተመላክቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶቾ እና ስፖርት ቢሮ የማህበረሰብ ስፖርት ማስፋፊያና ማደራጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል የስፖርት ፌስቲቫሎች እና ትርኢቶች መዘጋጀታቸው ስፖርትን በከተማ ደረጃ ለማስፋፋት እና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚረዳ አሳውቀዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.