ለታዳጊዎች ሴት የስፖርት ሰልጣኞች የሥነ ተዋልዶ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ለታዳጊዎች ሴት የስፖርት ሰልጣኞች የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ላይ የሚያተኩር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ለታዳጊዎች ሴት የስፖርት ሰልጣኞች የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ላይ የሚያተኩር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ታህሳስ 27 ቀን 2017 ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአምስቱም የስፖርት ትምህርታና ስልጠና ማዕከል ለሚሰለጥኑ ሴት ታዳጊ ስፖርት ሰልጣኞች የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚያተኩር ስልጠና ሰጥቷል

በስልጠናው በታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር የሚሳተፉ ሴት ስፖርተኞቸ መሳተፋቸው የገለጹት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል የሕክምና ቡድ መሪ ወይዘሮ ሐያት ኪያር ስነ ተዋልዶ ጤና ጥራትና ተደራሽነት በተመለከተ ኬኔሰፍ ኢትዮጵያ ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ገጸዋል፡፡

በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ያለው የመረጃ እጥረት ብዙ ታዳጊዎችን ለተለያዩ ችግሮች እያጋለጠ ነው ያሉት ወይዘሮ ሐያት ታዳጊዎች በስነተዋልዶ ጤና ጉዳይ ከቤተሰቦቻቸው ከመህራን እና ከአሰልጣኞቸ ጋር በግልጽ እንዲነጋገሩ አሳስበዋል፡

ስልጠናውን የሰጡት ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ፈትለወርቅ ታዳጊ ወጣቶችን የስነ ለዋልዶ ጤናቸው ተጠብቆ በአካላቸው ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ግንዛቤ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን አሰገንዝበዋል፡፡

የወር አበባ ንጽህና አጠባበቅ፣ የመራቢያ ክፍሎች ካላስፈላጊ እርግዝና ፣ከኤች አይ ቪ ኤድስና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ሰፊ ገለጻ ተደርጎል።

የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለታዳጊዎች፤ ለወጣቶች፤ አገልግሎቱ በነፃ እንደሚሰጥ ሲሰተር ፈትለወርቅ ገልፀው

በአገር ውስጥ የወጡ ከስነ ተዋልዶ ጋር የተያያዙ ፖሊሲ፣ ስራቴጂዎች፣ ፓኬጆችና ጋይድላይኖች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.