እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን

የአቶ በላይ ደጀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ታህሳስ 28 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ከሁሉ አስቀድሜ ለመላው አዲስ አበባ ወጣቶች ፣የስፖርት ቤተሰቦች እና ለክረስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ!!!

ውድ የከተማችን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በመላው አገራችን ለሚከበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላምና እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን በማለት በራሴ እና አዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስም መልዕክቴን ሳስተላለፍ ልደቱ የድኀነት ተሰፋ ቃል የተፈጸመበት በመንፈሳዊ እና በባህላዊ ትውፊቶች ታጅቦ በደስታ፣ በፍቅር፣ በሰላም እና በታላቅ ድምቀት የሚከበረው በዓል መሆኑን በመግለጽ ነው፡፡

ብርሃነ ልደቱን ሰናከብር ሰበአ ሰገል ልዩ ልዩ ገጸ በረከቶችን አምሃ ይዘው በቤተልሄም እንደተገኙ ሁሉ እኛም ባለን እውቅት፣ በተሰጠን ሐብት አገራችን ልናገለግል ይገባል።

ኢየሱስ ፍጹም በሆነ ትህትና በበረት መተኛቱ ግርግምን ሳይንቅ መታየቱ ለእኛ ትልቅ ትምህርት መሰረት በማድረግ ዝቅ ብሎ መስራትን በመለማመድ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም በንጽህና ተጥብቆ መኖር በማሰብ እኛም ህሊናችንን ንጹህ በማድረግ የሚታዩ ታላላቅ የለውጥ ቱሩፋቶችን በመቀበል ሊሆን ይገባዋል፡፡

ብርሃነ ልደቱ ፈጣሪና ፍጡርን ወሰን በሌለው ፍቅር የወደደበት፣ የሰው ልጆች ሁሉ አንድ የሆኑበት፣ መላእክትና ሰው የተስማሙበት፣ ሰማይና ምድር የታረቁበት የጥል አጥር የፈረሰበት እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስተምራሉ፡፡

ይሄ ታላቅ አስተምሮ ለከተማችን ወጣቶችና ስፖርት ቤተሰቦች የሚያስተላልፈው ትልቅ መልዕክት በስምምነት፣ በእርቅ፣ በአንድነት እና በፍቅር በመደመር ለአገራችን እድገትና ብልጽግና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

የነገ አገር ተረካቢ የሆናችሁ ውድ ወጣቶች አዲስ አበባ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በልማት ወዳድ ህዝቦቿ ጥረት አዳዲስ ነገሮችን የመስራት ጉጉትና ከፍተኛ የመለወጥ ፍላጎት በአስገራሚ ፍጥነት ስሟን የሚመጥን ውብ ገጽታ እየተላበሰች መገኘቷ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በዚህ ፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ ድንቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከታችሁ ሁሉ ልማቱን እንደ አይናችሁ ብሌን በመጠበቅ ባለቤት መሆናችሁን ማስመስከር አለባችሁ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ድምቀት የሆናችሁ የስፖርት ቤተሰቦች እናንተን ማዕከል በማድረግ እየተገነቡ የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የፈጠረላችሁን መልካም እድል በመጠቀም በተሰሩ የኮሪደር ልማቶቻችን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ የማድረግ ኃላፊነነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ በቢሮው እና በራሴ ስም ለብርሃነ ልደቱ እንኳን አደረሳችሁ ስል በከተማችን የሚገኙ ወጣቶችና የስፓርት ቤተሰቦችን ማኅበራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የስፓርት ልማት ዘርፍን ለማገዝ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የጀመርናቸው ስራዎች እንደምናጠናክር በማረጋገጥ ነው፡፡

በመጨረሻም የልደት በዓልን ስናከብርር የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ እና ፍፁም ኢትዮጵያዊ ባህል የሆነውን ወንድማማችነትንና እህትማማችነት በማጎልበት ፍቅራችን በማጠናከር አንድነታችንን በማድመቅ ይሁን እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣የፍቅር እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ።

አቶ በላይ ደጀን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

ምናልባት የ1 ሰው ምስል

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.