የቢሮውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም የስራ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የቢሮውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም የስራ ክፍሎች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። ወ/ሮ መቅደስ አዱኛ

የቢሮውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም የስራ ክፍሎች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። ወ/ሮ መቅደስ አዱኛ

ጥር 02 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደረገ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የቢሮው የፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መቅደስ አዱኛ የቢሮውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም የስራ ክፍሎች ሀላፊነታቸውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በቢሮው ኮሙኒኬሽን፣ ፋይናንስ እና ግዥን ጨምሮ 10 ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች እንዳሉ የገለፁት ወ/ሮ መቅደስ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋን ስፖርት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል።

የቢሮው ኦዲት፣ ህንፃ አስተዳደር፣ የለውጥ ስራዎች እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬቶች የበጀት አመቱን የ6ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት ተደርርጎባቸዋል

በተጨማሪም በውይይቱ የተቋሙ የስራ ዲስፒሊን ምን መምሰል እንዳለበት የተዘጋጀ ሰነድ በቢሮው የእቅድ እና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታቸው አበባየሁ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.