
ቢሮው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ቢሮው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ጥር 3 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂዷል።
ቢሮው የወጣቶችን ማህበራዊ፣ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ውጤታማ ስራዎች በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የገለጹትየቢሮ ወጣት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልድሃና ባሉን ጸጋዎች ለወጣቱ ስራ እድል ግንዛቤ ለመፍጠር እና አመለካከት ቀረጻ በስፋት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል
በወጣት ማብቃት እና በግንዛቤ ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት ወጣቶች ለአገር ልማትና እድገት አስዋፆኦ እንዲያበረክቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የገለጹት አቶ መክብብ በቀሪ ግማሽ ድክመቶችን በማረም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል በሁሉም መዋቅር በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል
የወጣቶች አቅምና አመለካከት ክፍተቶችን በጥናት በመለየት፤ ወጥነት፣ ተከታታይነት፣ደረጃውን የጠበቀና ለውጤት የሚያበቁ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ከመስጠቱ ባሻገር የወጣቶች የአገር ፍቅር ስሜትን ለማጎልበት የሚሰሩ ስራዎች በቀሪ ስድስት ወራትም በስፋት እንደሚሰሩ ተገልጽዋል
የወጣቶች አቅምና አመለካከት ክፍተቶችን በጥናት በመለየት፤ ወጥነት፣ ተከታታይነት፣ ደረጃውን የጠበቀና ለውጤት የሚያበቁ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠታቸው በመድረኩ የተወሳ ሲሆን የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ለወጣቶች ሳቢ ለማድረግ እና አገልግሎቶች የወጣቶችን ፍላጎት የሚመጥኑ እንዲሆኑ መሰራት የሚገባቸው ምክረ ሐሳቦች ቀርቧል
በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ያሉ ችግሮች ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ በሪፎርም የሚመለሱ ጥያቄዎች ማሳወቅ ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር ቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በትኩሩት መስራት በተሰሩ ስራዎች ሳንኩራራ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ማድረግ የትኩሩት አቅጣጫዎች መሆናቸው ተመልክቷል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.