የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የበርካ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የበርካታ ታቦታት ማደሪያ የሆነውን የጃን ሜዳ አከባቢ አፀዱ።

የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የበርካታ ታቦታት ማደሪያ የሆነውን የጃን ሜዳ አከባቢ አፀዱ።

ጥር 08 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የከተማውን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በማስተባበር ለጥምቀት በዓል በርካታ ታቦታት ማደሪያ የሆነውን የጃን ሜዳ አከባቢ ፅዳት አካሄደ።

በፅዳት ፕሮግራሙ ከ2ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች፣የስፖርት ቤተሰቦች፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮችን እና የአከባቢው ነዎሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል።

የጥምቀት በዓል በአለም በማይዳሱ ቅርስነት የተመዘገበ የኢትዮጵያን መገለጫ በዓል በመሆኑ ሀይማኖታዊ ቱፊቱን በጠበቀ በአማረ እና በደመቀ መልኩ ለማክበር የተዘጋጀ የፅዳት ዘመቻ ስራ መሆኑን አቶ ጤናየ ታምሩ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ተወካይ ተናግረዋል።

ጥምቀት በጉጉት የምንጠብቀው በዓላችን ነው ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ የሀይማተኖት ተቋማት ጉባኤ የወጣቶች እና ሴቶች መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ራምላ ከድር ሲሆኑ የበዓሉ ባለቤቶቹ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቢሆኑም የጥምቀት በዓል የመላው ኢትዮጵያውያን ሀብት በመሆኑ ሁላችንም በዓሉ በአማረና በደመቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር ሀላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

በፅዳት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ወጣትች እና የስፖርት ቤተሰቦቸም የጥምቀት በዓል አብሮነትን፣ አንድነትን እና ወድማማችነትን የሚያጠናክር እና በርካታ የውጭ ቱሩስቶች የሚታደሙበት የአደባባይ በዓል በመሆኑ ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሀላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.