15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫልና ተጠናቀቀ

15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫልና ተጠናቀቀ

ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለተከታታይ ለ4 አመታት አጠቃላ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት ከታህሳስ 26 ጀምሮ ለሁለት ሳምታት ሲካሄድ የሰነበተው 15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ ሲጠናቀቅ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለተከታታይ 4 አመታት አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ችሏል።

የባህል ስፖርት ለሕረ ብሔራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በተካሄደው ደማቅ የመዝጊያው ሥነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን ጨምሮ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የባህል ስፖርት የፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና የአስረ አንዱም ክፍለ ከተማ ስፖርት ልዑካን ታድመዋል፡፡

ባህል ስፖርቶቻችን የአብሮነት የወድማማችን፣ የእትማማችነት፣ የህብረ ብሄራዊነት መገለጫችንና የአንድነት መተሳሳሪያችን ናቸው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባህል ስፖርትን ለማጠናከር የሚደረጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

15ኛዉ ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች እና ፌስቲቫል የባህል ስፖርቶች ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን 11ዱም ክፍለ ከተሞች በ9 የስፖርት አይነት ከ10ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈዉበታል፡፡

የስፖርት ፖሊሲያችን ሁሉን አቀፍ በመሆኑ በተለይ ለዛሬዉ ዘመናዊ ስፖርቶች መሰረት የሆነዉ የባህላዊ ስፖርታችን ይበልጥ ለማጉላትና ተሳትፎዉን በማህበረሰባችን እና በታዳጊ ወጣቶች ለማስረፅ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ በላይ ገልጸዋል፡፡

በ15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በሁለቱም ፆታዎች በተካሄዱ 9 የስፖርት አይነቶች አሸናፊ ለሆኑ ክፍለ ከተሞች የዋንጫ ሽልማታቸውን ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል

ለሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ፉክክር ሲደረግብት በቆየው ውድድሩና ፌስቲቫልን ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሁሉም ስፖርት አይነት 24 የወርቅ ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 2ኛ የውድድሩ አስተናጋጅ ቦሌ ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በውድድር ፌስቲቫሉ በሽብርቅ በተሳትፎ በስፓርታዊ ጨዋነት አሸናፊ ክፍለ ከተሞች የዋንጫ ሽልማት ከበርከቱ ባሻገር የገና ስፓርትን ለማስተዋወቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ በውድድሩ ለተሳተፉ ስድስት ክፍለ ከተሞች የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።

በ15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርት ውድድር በተሳትፎ ለሚ ኩራ 1ኛ ልደታ 2ኛ አራዳ 3ኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ በስፖርታዊ ጨዋነት ልደታ ክፍለ ከተማ የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ ሆኗል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.