በስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት የከተማ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት የከተማ ግብርና መስፋፋቱ በታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ላይ አዋንታዊ ወጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ።

 

በስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት የከተማ ግብርና መስፋፋቱ በታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ላይ አዋንታዊ ወጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ።

ጥር 15 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማው በሚገኙ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ላይ የከተማ ግብርናን ማስፋፋቱ በታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ላይ አውንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት በከተማ ግብርና የሚገኙ ምርቶችን በማዕከላቱ በልዩ የስፖርት ስልጠና ለሚሰለጥኑ ታዳጊዎች እንደሚውል ገልፀዋል።

በልዩ ስልጠና ጣቢያዎች ለሚሰለጥኑ ታዳጊዎች በከተማ ግብር በሚገኝ ምርት ምገባ መጀመሩ ታዳጊዎችን በአካል እና በአእምሮ እንዲዳብሩ ከማድረጉ በላይ የሚሰጣቸውን ስልጠና በብቃት እንዲሰለጥኑ በማድረግ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛት ለማፍራት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን አቶ በላይ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከዮኒሴፍ ኢትዮጵያዊ በተገኝ ገቢ ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና የሚውል የከተማ ግብርናን በጃን ሜዳ፣ በራስ ሀይሉ እና በአበበ ቢቂላ የስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት ማስጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን የቢሮው እና ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የመጡ አመራሮች በማዕከላት እየተሰሩ ያሉ የከተማ ግብርና ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+7

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

117አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 116 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.