
ተቋርጦ የቆየው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ
ተቋርጦ የቆየው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ
ጥር 17 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስፖርት ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ስቴድየም በደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀመሯል
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባት ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ፖሊስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከተ ተናግረው የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድሮችን ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
ዜጎች በሰላም ወጠው እንዲገቡ፣ የተለያዩ ሀገራዊና አለም አቀፍ ሁነቶች ካለምንም የፀጥታ ችግር በመዲናዋ እንዲካሄዱና አዲስ አበባ የሰላም ተምሳሌት ከተማ እንድትሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ እየሰራ ያለው ስራ የሚደረቅ መሆኑን አቶ ሞገስ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው የአንድ አገር ሁለንተናዊ ህልውና ለማረጋገጥ እና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚያስፈልጉት መሰረታዊ ተቋማት መካከል የጸጥታ ዘርፍ ቀዳሚ መሆኑን ገልጸው የአዲስ አበባ ፓሊስ የመዲናዋን ጸጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ በልማት፣ በሰላም እና በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እያደረገ የሚገኘውን ተሳትፎ ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል።
ስፖርት እና ፖሊስ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ያሉት አቶ በላይ ብቁ፣ንቁ እና ለማንኛዉም ተልዕኮ ዝግጁ የሆኑ የፖሊስ ስራዊትን ለማፍራት ስፖርትን ባህል ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ከለውጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በ8 የስፖርት አይነት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚካሄድ የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የፖሊስ ስፖርት ውድድር እና ፌስቲቫል መዘጋጀቱ ከስፖርታዊ ውድድሩ ባለፈ በአባሉ ዘንድ አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ወድማማችነት እና እህትማማቸነት ስሜት በመፍጠር ጠንካራ የፖሊስ ተቋም ይገነባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ስም እና ሰንደቅ አላማ በአለም የስፖርት የውድድር መድረክ ከፍ ያደረጉ ስፖርተኞች ከፖሊስ አባላት እንደወጡ ያስታወሱት ኮሚሽነር ጌቱ በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በመክፈቻ ፕርግራሙ የተለያዩ የፖሊስ የሰልፍ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን የገመድ ጉተታ እና የእግር ኳስ ውድድሮችም ተካሂደዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.