
ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ። አቶ በላይ ደጀን
ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ። አቶ በላይ ደጀን
ጥር 18 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኝውን መላጣ ሜዳን ጎበኙ።
የሜዳው ግንባታ በተቀመጠለት ስታዳርድ መሰረት ደረጃውን ጠብቆ እየሰራ መሆኑንን አቶ በላይ የገለፁ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለአከባቢው ማህበረሰብ በተለይ ለታዳጊዎች እና ለወጣቶች አገልግሎት እንዲሰጥ ክፍት ይደረጋል ብለዋል።
የአከባቢው ወጣቶች ከስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ጥያቄ በተጨማሪ የወረዳው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ይታደስልን፣ የስራ እድል ይመቻችልን እና የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ ይደረግልን የሚሉ ጥያቄዎች እንደነበራቸው ያስታወሱት አቶ በላይ አሁን ሁሉም ጥያቄዎቻቸው በሚባል ደረጃ ቀስ በቀስ እየተመለሱላቸው መሆኑን ገልፀዋል
ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን የዘወትር ጥያቄ የነበረውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ በላይ ገልፀው በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከ1321 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
የኮልፌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው የመለጣ ሜዳ በአማረና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለመገንባት ለአከባቢው ማህበረሰብ በምርጫ ወቅት ቃል ተገብቶ እንደነበር አስታውሰው መንግስት ቃል በገባው መሰረት ፕሮጀክቶችን እያጠናቀቀ ለህብረተሰቡ እያስረከበ ለመሆኑ ይህ ሜዳ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
በክፍለ ከተማው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ዋስ ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።
የአከባቢው ታዳጊዎች እና ወጣቶችም የመላጣ ሜዳ በአማረና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተገነባ መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልፀው የነበረባቸውን የሜዳ ችግር እንደሚፈታላቸው ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራን ጨምሮ ያሏቸውን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየፈታላቸው በመሆኑን የአከባቢው ወጣቶች ተናግረዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.