
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ እናትነት በሚል መሪ ቃል በኮልፌ ክፍለ ከተማ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ እናትነት በሚል መሪ ቃል በኮልፌ ክፍለ ከተማ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ
ጥር 18 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ እናትነት በሚልጨመሪ ቃል በኮልፌ ክፍለ ከተማ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ አመራሮች እና ነዋሪዎች በተገኙበት የብዙሀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤናማ እናትነት ወር ስናከብር በወሊድ ወቅት እና ከወሊድ በኋላ በእናቶች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት በመከላከል በኩል የጤና ባለሙያዎችንና ሌሎች የእናቶች ጤና አገልግሎት ዘርፍ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ በማድረግ ነው ብለዋል።
እናት ህይወት ለመስጠት ህይወት ማጣት የለባትም ያሉተሰ ዳ/ር መቅደስ በአለም ለ38ኛ ጊዜ በሀገር ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የእናትነት ወር ዋና አላማው የእናቶች ሞትና ህመም ለመቀነስ እንዲቻል ግንዛቤ ለማስጨበጥ በመሆኑ ይህም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የዚሁ አንድ አካል መሆኑን አሳውቀዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው እናት ከፅንስ ጀምሮ በሆዷ ተሸክማ፣ ማንም የማይጋራትን አስጨናቂ ምጥ አምጣ ወልዳ ለቁም ነገር የማብቃት ጥንካሬ ከፈጣሪ የተሰጣት እናት ነች ብለዋል።
በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብ እንዲሁም በመንግስት ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶ የእናቶችን ህመምና ሞት ለመቀነስ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸው ለዚህም ተግባር ሁሉም ተባባሪ አዠእንዲሆን ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለጽ በዚህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተሳተፍን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ነዋሪዎች ለተግባሩ መሳካት የበኩላችንን ሀላፊነት ልንወጣ ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.