
የስፓርት ዘርፉን ለማሻሻል እና የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ /አቶ በላይ ደጀን/
የስፓርት ዘርፉን ለማሻሻል እና የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ /አቶ በላይ ደጀን/
ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የቅንጅት እና ትብብር ስራዎችን ገመገመ
ጥር 19 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት በቅንጅት እና ትብብር የመልካም አስተዳዳር አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
በውይይቱ ቢሮው በበጀት አመቱ በቅንጅት ለመስራት የተፈራረማቸው የተቋማት ሀላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ የወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች እና የቢሮው የፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተሳትፈዋል።
ከተቋማት ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ውጤታማ ለማድረግ ወቅቱን የጠበቀ ውይይት ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ያወሱት የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሴክተር የወጣቱን ጉዳይ አብይ አጀንዳ በማድረግ የሰሩት ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ባለፈት ስድስት ወራት ከ15 ሴክተር ተቋማት በ29 ተግባራት በቅንጅትና ትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውሰው የስፓርት ዘርፉን ለማሻሻል እና የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ቢሮው በአገልግሎት ሰጪ እና ተቀባይ መካከል የእርካታ መስተጋብር ለመፈጠር የለያቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ በላይ በወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት ፍትሃዊ እና አካታችነት አሰራር ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በወጣቶች ማህበራዊ፣አኪኖሚያዊ እና ፓለቲካው ቅንጅታዊ አሰራር በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ያወሱት አቶ በላይ የወጣት ማዕከላት ጣልቃ ገብነትን በስፓርት ማዘውተርያ ስፍራዋች አጠቃቀም እና የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለማሟላት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በመንፈቀ ዓመቱ ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉት መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልሐሚድ ድሌቦ የሴክተር ተቋማት ተሳትፎ አበረታች በመሆኑ ውጤታማ ስራዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል
የሚያጋጥሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መሰራቱን ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አቶ አብዱላሚድ በስድስት ወር የትስስር አሰራር ትግበራ አፈጻጸም ስኬታማ መሆናቸውን ገልጸዋል
የውይይቱ ተሳታፊዋችበሰጡት አስተያየት ቢሮው ያዘጋጀው ግምገማ ወቅታዊ እና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም አካል ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።
ቢሮው በ2017 የመጀመሪያ 6ወራት በቅንጅት አሰራር ጥሩ ወጤት ላመጡ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
185You፤ Gossaye Alemayehu፤ Dan Smst እና 182 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.