
ቢሮው በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈፃፃም ሪፖርት ዙሪያ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።
ቢሮው በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈፃፃም ሪፖርት ዙሪያ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።
ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ከሰራተኞች ውይይት አካሄደ።
የምናገለግለውን የስፓርት ቤተሰብና ወጣቱን እርካታ ከፍ በማድረግ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩሩት መስራት እንደሚገባ ያወሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልድሃና የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ ስፓርቱን ለማስፋፋት በቀሪ ስድስት ወራት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ በበኩላቸው ያሉንን ግቦች ስኬታማ ለማድረግ በቅንጅትና ትብብር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው በቢሮው የተጀመረ የስራን ቦታ ምቹ የማድረግ እንቅስቃሴ በየደረጃው ባለው መዋቅር መተግበር እንደሚገባ አመላክተዋል።
በቢሮና በማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎት ውጤታማ የሚሆነው ባለሙያውም ስማርት ሲሆን ነው ያሉት የቢሮ አማካሪ አቶ ታሪኩ እሸቴ በቀሪ ስድስት ወራት ተቋማዊ አስራርን በመዘርጋት በስፓርት እና በወጣት ዘርፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ሰፊ ገለጻ ያደረጉት የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ የወጣቶች ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ተግባሮች ማከናወኑን ገልጸዋል
በከተማ ደረጃ የስራ እድል ካገኙ ውስጥ 80 ከመቶ ወጣቶች መሆናቸው የገለጹት አቶ ጌታቸው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፣ በስፓርት ትርኢት፣በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባህል በማድረግ እና በአገልግሎት አሰጣት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አስታውሰዋል
በማብቃት፣በተጠቃሚነት፣በተሳትፎና ውድድር እንዲሁም በማዘውተርያ ስፍራ ልማት በቀጣይ ስድስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ አቶ ጌታቸው ገለጻ አድርገዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.