በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ስፖር...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ስፖርታዊ ውድድር ጥር 22 ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ስፖርታዊ ውድድር ጥር 22 ተጀመረ

ጥር 20 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርታዊ ውድድር ጥር 22 ይጀምራል

ውድድሩን አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ካምባስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዳ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር መካሄዱ ከውድድር ባለፈ በተማሪዎች ዘንድ አንድነትን፣ አብሮነትን፣ ወድማማችነትን እና እህትማማችነትን ያጠናክራል ብለዋል።

በአካል እና በአእምሮ የዳበረ ትውልድን ለመፍጠር እንዲሁም በዩኒቨርስቲዎች ስፖርትን ባህል ለማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ዳ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ በበኩላቸው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የዩኒበርስቲ ተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ውድድሩም በ6 የስፖርት አይነት በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በቮሊብል፣ በቼስ፣ በፖራሊፒክ እና በአትሌቲክስ የስፖርት አይነቶች እንደሚካሄዱ የገለፁት አቶ ዳዊት ከጥር 22 እስከ የካቲት 02/2017ዓ.ም ይካሄዳል ብለዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ፕሮግራም ላይ የእጣ ማውጣት ስነ-ስዓትም ተካሂዷል።

+4

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.