ቢሮው ባለፉት 6 ወራት በሰጠው የግንዛቤ ማስጨበ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ቢሮው ባለፉት 6 ወራት በሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ113ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።

ቢሮው ባለፉት 6 ወራት በሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ113ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከከተማ እስከ ወረዳ ካሉ የቢሮ ማዋቅር አመራሮች ጋር ተወያየ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የወጣቶችን ማሕብራዊ፣ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በመፈቅ አመቱ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

ቢሮው በስራ እድል ፈጠራ ላይ በሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ113ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው የተናገሩት አቶ በላይ በድግግሞሽ ከ4 ሚሊየን በላይ የከተማው ነዋሪዎች በማህበረስ አቀፍ የአካል እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙ የኮሪደር ልማቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አካተው መሰራታቸው የከተማው ወጣቶች የዘወትር ጥያቄ የሆነውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ እጥረት እየቀረፈ እንደሚገኝ የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።

ከ58ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በከተማው በሚገነቡ የኮሪደር ልማቶች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ በላይ ወጣቶች በከተማዋ የልማት እና ሰላም ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።

የቢሮውን የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቶ ጌታቸው አበባየሁ የእቅድ፣ በጀት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዋል።

በሪፖርቱ ቢሮው የውጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከመገንባት፣ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ከመፍጠር፣ ስፖርታዊ ውድድሮችን እና ፌስቲቫሎችን ከማካሄድ አኳያ ያከናወናቸው ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩ ከእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በተጨማሪ በተመረጡ ክፍለ ከተማች፣ ወረዳዎች እና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተካሄደ የኢንስፔክሽን ሪፖርት እንዲሁም የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ክትትል እና ድጋፍ ግብረ መልስ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች እና ሀሶቦችም የቢሮው አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.