የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የተማሪዎች የስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የተማሪዎች የስፖታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ተጀመረ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የተማሪዎች የስፖታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ተጀመረ

ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ስፖርት ለሁለንተናዊ ሰብዕና በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ዛሬ በ6 ኪሎ ካምፓስ በድመቀት ተጀመሯል

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ኃላፋች እንዲሁም ተማሪዎች ተገኝተዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በሚካሄደው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል 12 ኮሌጆች በ6 የስፖርት አይነት በሁለቱም ፃታ የሚሳተፋበት ይሆናል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ስፓርት ለጤና ለፍቅር ለአንድነት ካለው ፋይዳ ባለፈ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አገራዊ ሕብረትንና አንድነት ለማስፋፋት ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአገራችን ስፖርት እድገት ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ጀምሮ በውድድር፣ በሳይንሳዊ ስልጠና እና በሁሉን አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ትልቅ አሻራ ማሳረፉን የገለጹት አቶ በላይ በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስፖርትን ለማህብራዊ ልማት እና ለአገር ብልጽግና ለማዋል፣ አዲስ አበባን የዘመናዊ እና የባህላዊ ስፓርት ማዕከል ለማደረግ በየደረጃው የሚያከናውነው ዘርፈ ብዙ ተግባር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አቶ በላይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድሮች መዘጋጀታቸው ከውድድር ባለፈ በተማሪዎች ዘንድ አንድነትን አብሮነትን፣ወዳጅነት፣ሕብረ ብሔራዊነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ይፈጥራል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ባለፈው አመት የሁለትዮሽ ስምምነት እንደተፈራረሙ ያስታወሱት ዳ/ር ሳሙኤል ለከተመው ብሎም ለሀገር የስፖርት እድገት የሚበጁ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በመክፈቻ ፕሮግራም የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር በአዲስ አበባ ህንፃ ኮሌጅ እና ከአዲስ አበባ ቢዚነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መካከል የተካሄደ ሲሆን ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጀሰ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎል።

ቀጣይ ጨዋታዎቸ ከነገ ጀምሮ በ6ኪሎ ካሞፖስ እና በሌሎች ኮሌጆች የሚካሄድ ይሆናል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.