
ከተማ አስተዳደሩን ወክለው በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ለሚሳተፈው የልዑካን ቡድን አባላት ደማቅ ሽኝት ተደረገላቸው።
ከተማ አስተዳደሩን ወክለው በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ለሚሳተፈው የልዑካን ቡድን አባላት ደማቅ ሽኝት ተደረገላቸው።
ጥር 24 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክለው በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ ከተማ በሚካሄደው 8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ላይ ለሚሳተፉ የልዑካን ቡድን አባላት ደማቅ ሽኝት ፕሮግራም ተደረገላቸው።
በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን አዲስ አበባን ከውድድር ባለፈ በአምባሳደርነት ጨምር ወክላችሁ የምትሄዱ በመሆኑ የመዲናችሁን መልካም ገፅታ ገንብታችሁና አስተዋውቃችሁ መምጣት ይኖርባችኋል ብለዋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12 የስፖርት አይነቶች ከ450 በላይ የልዑካን ቡድን አባላትን በውድድሩ እንደሚያሳፍ የገለፁት አቶ በላይ ስፖርተኞች በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እና አሸናፊነት ስሜት በመላበስ የከተማ አስተዳደሩን ስም እንዲያስጠሩ ከአደራ ጭርምር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች መቀመጫ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከመሆኗም በላይ የአብሮነት፣ የአንድንድነት፣ የህብረ ብሔራዊት እና የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ መሆኗን የምናሳይበት ውድድር ነው ሲሉ የቢሮው ሀላፊው ገልፀዋል።
የልዑካን ቡድን አባላቱም በውድድሩ ጥሩ ውጤት ይዘው እንደሚመለሱ የገለፁ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩን መልካም ስም በሁሉም መንገድ ለማስጠራት እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።
የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ ሀገር በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጋ ወጣቶች ምዘና ውድድር በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ ሶድ ከተማ ከጥር 27 እስከ የካቲት 04/2017 የሚካሄድ ይሆናል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.