
8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር በደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀመረ።
8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር በደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀመረ።
ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ ሀገር በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሶዶ ከተማ በደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀመረ
በመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የኢፌድሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አማካሪ አቶ ቀጀላ መረዳሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉን ጨምሮ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት እና የክልሉ ነዋሪዎች በስፋት ታድመውበታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ልዑክ ቡድን የአዲስ አበባን መልካም ገፅታ የሚገነቡ በተለይ አዲስ አበባ ውብ አዲስ እና ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረው የሚኖርባት ከተማ መሆኖን ለታዳሚያን አሳይተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ለስድስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው አገር አቀፍ የታዳጊዎች ምዘና ውድድር በክልሉ መካሄዱ እንዳስደስታቸው ገልጸው፤ ውድድሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጣነውን የተተኪ ስፓርተኛ ችግር የሚፈታ ነው ብለዋል
እንዲህ አይነት ውድድሮች የኢትዮጵያን በስፓርቱ መስክ አሸናፊነቷን የሚያስቀጥሉ ናቸው ያሉት አቶ ጥላሁን ውጤታማነት ለማረጋገጥ እና በሁሉም የስፓርት መስክ ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል
በመክቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ መንግስት ለስፓርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት በፌደራል በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የማዘውተርያ ስፍራዎችን በመገንባት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
የስፓርት መሰረት ልማት መስፋፋት ለታዳጊ ወጣቶች መልካም እድል ነው ያሉት ሚንስትሯ በ2017 በጀት ዓመት ተቋርጠው የቆዩ ውድድሮች ከማስጀመር ባሻገር ልዩ ልዩ ዓመታዊ ውድድሮች ለማካሄድ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል
12 ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳድሮች በ11 የስፓርት አይነት ከፍተኛ ፋክክር የሚያደርጉበት አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ለተከታታይ አስር ቀናት እንደሚቀጥል ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
132Gossaye Alemayehu፤ Dawit Dave እና 130 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.