"ብልጽግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

"ብልጽግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የወጣቶች ፌስቲቫል በልደታ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

"ብልጽግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የወጣቶች ፌስቲቫል በልደታ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

ጥር 25 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ብልጽግናና አብሮት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የወጣቶች ፌስቲቫል በሜክሲኮ ኮሪደር በርካታ ተሳታፊ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት ተካሄደ

በፌስቲቫሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ ወጣቶች ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ ከማሳለፍ በመቆጠብ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በመገኘትን ለህይወታችሁ አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችንና ትምህርቶችን እንዲሁም ልምዶችን በመቅሰም ለሀገር ባለውለታ ልትሆኑ ይገባል በማለት ገልፀዋል

አቶ ክብርዓለም ደምሴ አያይዘው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ወጣቶችና ታዳጊዎች ከአልባሌ ቦታ እርቆ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ እየተዝናኑ በአይምሮና በስብዕና በመልካም ለመቅረፅ ታሳቢ ያደረገ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል በማለት ገልፀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ያዘጋጀው የወጣቶች ፌስቲቫል በርካታ ፕሮግራሞች በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በሚሰሩ ወጣቶች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዘመናዊና ባህላዊ ውዝዋዜ፣ ቲያትር፣ ግጥም፣ ሙዚቃዎች፣ ቴኳንዶና ውሹ እንዲሁም በማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል።

የፌስቲቫሉ ታዳሚዎችና አቅራቢ የሆኑ ከ9ኙም ማዕከላት የተገኙ ወጣቶችና የአከባቢው ማህበረሰብ በሰጡት አስተያየት እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች የወጣቱን ስነ-ምግባር በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና ስላላቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ሌሎች ወጣቶችም ወደ ማዕከላት በመምጣት እንዲሳተፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

ልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.