የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ፌስቲቫል ተካሄደ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ፌስቲቫል ተካሄደ

ጥር 25 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ስፖርት ጽ/ቤት የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን " ብልጽግና አብሮነት በማዕከላት ፍሬዎች ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል የወጣቶች በ ፌስቲቫል ተካሄደ።

በክፍለ ከተማው በ10ሩም ወረዳ የሚገኙ የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከላት ላይ የሚሳተፉት ቡድኖች የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች አቅርበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ተክሌ እንደተናገሩት የመርሃ ግብሩ ዓላማ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በተለያዩ ክበባት ታቅፈው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ተሰጥኦዎቻቸወንና ስራዎቻቸውን እንዲሁም በማዕከላት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለብዙሃን ወጣቶችና ህብረተሰብ ክፍሎች ማስተዋወቅ እንደሆነ ተናግረዋል።

በጽ/ቤቱ የወጣቶች ማብቃት ቡድን መሪ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ በበኩላቸው ወጣቶች ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚፈጥሩበት ሁኔታ በማመቻቸት የመቻቻል የመከባበር ባህልን አዳብረው በጋራ ዓላማ እንዲሰለፉ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

በስብዕና ማዕከላት ላይ በተደረገው የተለያዩ ዘመናዊ ዳንስ ፣ ባህላዊ ውዝዋዜ ፣ ቴክዋንዶ ፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ቀርበውበታል።

ብልጽግና አብሮነት በማዕከላት ፍሬዎች ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል መሪ ቃል የተሳተፉ ቡድኖች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ጉለሌ ክኬፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.