
ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።
ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።
ጥር 25 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ "ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል አካሄዷል።
በፌስቲቫሉ ህፃናትና ወጣቶች በዘመናዊ ዳንስና በባህላዊ ውዝዋዜ የነበራቸውን ተሰጥኦ ለታዳሚው ያሳዩ ሲሆን በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው ፌስቲቫል ተወዳዳሪ የሚሆኑ አማተር ቡድኖችን አወዳድሮ በመሸለም ይበልጥ እንዲዘጋጁ አድርጓል።
ውድድሩን ከአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቲያትርና ባህል ተቋም የመጡ ታዋቂ ዳኞች ዳኝተውታል።
ፌስቲቫሉን የከፈቱት የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጠብቀው አመሸ የወጣቶችና ህፃናትን ስብዕና በመገንባት የተለያየ ተሰጧቸውን እንዲያጎለብቱ ማድረግ የጽ/ቤቱ አንዱ ተልዕኮ መሆኑን ገልፀው ይህንን ታሳቢ ያደረገ ስራ በ10ሩም የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ወጣቶችና ህፃናት ይህንን እድል ተጠቅመው ተሰጧቸውን ሊያጎለብቱ ይገባል ያሉት አቶ ጠብቀው የዛሬው ተወዳዳሪዎች ላቀረባችሁት ትልቅ ስራ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
በቀጣይም በከተማ ደረጃ በሚካሄደው ፋስቲቫል ላይ በብቃት ተወዳድራችሁ ቂርቆስን እንደምታስጠሩ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል አቶ ጠብቀው በመልዕክታቸው
ቂርቆስ ኮሙኒኬሽን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.