"ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

"ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ፌስቲቫል በአራዳ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል

"ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ፌስቲቫል በአራዳ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል

ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

"ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ፌስቲቫል በአራዳ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ በፌስቲቫሉ መጀመሪያ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች በየአካባቢው ባሉ የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በመገኘትና በመሳተፍ ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን በማከናወን ጊዜያቸውን ሊያሳልፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታሁን አክለውም የወጣቶች ሁለ ገብ የስፖርት እንቅስቃሴ የቡድን ቅንጅትን፣ የአንድ ስፖርተኛ ዋጋ ለሁሉም ስፖርተኛ የሚጠቅም መሆኑን የሚያሳይ፣ ፍቅርንና ውህደትን እንዲሁም መደጋገፍን በአጠቃላይ የጋራ ድምቀትንና ውጤትን የሚያሳይ በመሆኑ በሌላው ሥራችንም ልንጠቀምበት የሚገባ ነው ብለዋል።

ብዙ ወጣቶች ያላቸውን ተስጥዖ ለማሳየት የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሚና የጎላ ነው ያሉት የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይልማ ተረፈ ጽ/ቤታቸው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በፌስቲቫሉ የተለያዩ ትዕይንቶች የቀረቡ ሲሆን የውዝዋዜ ውድድርም ተካሂዷል።

በመጨረሻ ዝግጅቱን ለደገፉ አካላትና በውዝዋዜ ከ1-3 ለወጡ ወጣቶች የምስጋናና እውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

አራዳ ኮሙኒኬሽን

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.