የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የአቋም መለኪያ ሻምፒዮና...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የአቋም መለኪያ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ

የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የአቋም መለኪያ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ

ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን ያዘጋጀው የ2017 ዓ.ም የክለቦች የአቋም መለኪያ ሻምፒዮና ዉድድር በጥበብ ኢንተርናሽናል ቴኴንዶ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

25 ክለቦች ጠንካራ ፉክክር ባሳዩበት በአጠቃላይ ውጤት ጥበብ ኢንተርናሽናል ቴኴንዶ ክለብ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ MDMR ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ 2ኛ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሦስተኛ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ

ቢ ሻምፒዮን ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ክለብ የስፓርታዊ ጨዋነት የጸባይ ዋንጫን ወስዷል

ውድድሩ የክለቦችን አቋም ከመለካት ባሻገር የእርስ በእርስ ትስስርን ያጠናክራል ያሉት የፌድሬሽኑ ፕሬዘዳንት ስፓርቱን በሚፈለገው ልክ ለማሳደግ የሚካሄዱ እንደዚህ አይነት ውድድሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል

በአራት ኪሎ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተካሄደው ውድድር ላይ ከ25 ክለቦች የተውጣጡ ከ350 በላይ ስፓርተኞች በ61 ካታጎሪ ከፍተኛ ፋክክር ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የውብዳር ጌትነት ነግረውናል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት ቸሩ ኩሳ በአልቲያስ ጅም ስም ስፓርቱን ለማነቃቃት ላበረከቱት የ20ሺ ብር ድጋፍ እእንዲሁም በውድድሩ የተሳተፉ ክለቦችን ጽ/ቤት ኃላፊዎ አመስግነዋል

በሁሉም ካታጎሪ በአጠቃላይ ውጤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ አሸናፊ ስፓርተኞች የሜዳልያ ሽልማት ከመበርከቱ ባሻገር ለኮከብ ዳኞች እውቅና መሰጠቱ ተመልክቷ

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.