
የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ማራኪ ማድረግ የምንፈልገው ወጣት በተፈላጊው ቦታ እንዲውል ያስችላል። አቶ በላይ ደጀን
የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ማራኪ ማድረግ የምንፈልገው ወጣት በተፈላጊው ቦታ እንዲውል ያስችላል። አቶ በላይ ደጀን
ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር እድሳት የተደረገለት የወረዳ 11 ወጣት ማዕከል ስራ የማስጀመሪያ እና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፌስቲቫል የመክፈቻ ስነ ስርዓት አካሄደ
"ብልጽግና እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴን ጨምሮ ሌሎች የከተማና የወረዳ አመራሮች እና የኪነ ጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የወጣቱን ማህበራዊ ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በመዲናዋ በተሰሩ የልማት ስራዎች አበረታች መሆኑን በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገልጸዋል
የነገ ሀገር ተረካቢው ትውልድ በራሱ ላይ ተንክሮ እንዲሰራና የተለወጠና ምክንያታዊ አስተሳሰብ እንዲይዝ የወጣት ማዕከላት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ መሆነቸውን አቶ በላይ ተናግረዋል ።
ኪነ ጥበብ የሀገርን ባህል እና እሴት ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ የማይተካ ሚና እንዳለው የገለፁት አቶ በላይ በዘርፋ ተተኪዎችን ለማፍራት ከታሰበ አማተር የኪነ ጥበብ ክበባትን መደገፍ እንደሚገባም አሳውቀዋል።
እድሳት ተደርጎለት ቁሳቁስ ተሟልቶለት አገልግሎቱን አዘምኖ ወደ ስራ የገባው የወረዳ 11 ወጣት ማዕከል በመልካም ሰብዕና የተገነቡ ወጣቶችን ለማፍራት ያስችላል ያሉት አቶ በላይ በእውቀትና ክህሎት የበለፀጉ እንዲሁም አዕምሮአዊና አካላዊ ጤናቸው የተጠበቀ ወጣቶችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ተጣናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል
ወጣቶች ጽንፈኝነት በመታገል የከተማ አስየዳደሩን ልማትና ሰላም በመጠበቅ ለሀገርና ለቤተሰብ አለኝታ መሆን አለባቸው ያሉት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የታለመላቸውን ግብ እንዲያሳኩ መደገፍ አለባቸው ብለዋል።
አቶ መብራቱ አያይዘውም ማዕከሉ ለወጣቶች ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ወጣቶች ጊዜያቸውን ለአገር በሚጠቅም ጉዳይ ለማስለፍ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እየተወጡ ያለው ሚና እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል
የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባረክ ደሊል በበኩላቸው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማከላትን ምቹና ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አውስተው ወጣቶች በኪነጥበብ፣ በስፖርትና በእውቀት ብቁና ተወዳዳሪ ባለ ተሰጦ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አበብልጽግና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚለው ሀሳብ በሚካሄደው ውድድር ባለ ተሰጥኦ ወጣቶችን ለማየት ያስችላል ያሉት አቶ ሙባረክ ውድድሩ ከተማ አስተዳደሩን የሚያጎሉ የፈጠራ ስራዎች የሚታይበት መሆኑን ጠቁመዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.