
የወጣቶችን አብሮነት፣ አንድነት፣ ወድማማችነትና እህትማማችነትን ለማጠናከር የወጣቶች ፌስቲቫል መዘጋጀቱ ሚናው የጎላ ነው። አቶ መክብብ ወ/ሀና
የወጣቶችን አብሮነት፣ አንድነት፣ ወድማማችነትና እህትማማችነትን ለማጠናከር የወጣቶች ፌስቲቫል መዘጋጀቱ ሚናው የጎላ ነው። አቶ መክብብ ወ/ሀና
ጥር 30 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ብልፅግናና አብነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል ቃል እያካሄደ የሚገኝው የወጣቶች ፌስቲቫል የመጨረሻ የማጣሪያ ውድድር በብሔራዊ ቲያትር እየተካሄደ ይገኛል።
በውድድሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መክብብ ወ/ሀና የወጣቶቸን አብሮነት፣አንድነት፣ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለማጠናከር ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እንዳሉ የተናገሩት አቶ መክብብ ማዕከላቱን ምቹ፣ ዘመናዊና ወጣቶች የሚያዘወትሩበት ስፍራ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በማዕከላቱ የሚገኙ የኪነጥበብ ክበባት ወጣቶች ተሰጧቸውን የሚያወጡበት እና ተተኪ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚረዳ ም/ቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።
ዛሬ በተካሄደ የመጨረሻ የወጣቶች ፌስቲቫል የማጣሪያ ውድድር 11 የባህላዊ ውዝዋዜ እና 11 የዘመናዊ ዳንስ ውድድሮች የቀረቡ ሲሆን በሁለቱም ዘርፍ ለፍፃሜ ውድድር ያለፉ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተለይተዋል።
በባህላዊ ውዝዋዜ 1ኛ አዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 3ቁ1 ኢትዬ ወግ የኪነጥበብ ቡድን 2ኛ ኮልፌ ክ/ከ ወረዳ 1 አንድ ኢትዮጲያ የኪነ ጥበብ ቡድን 3ኛ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 7 ህንደኬ የኪነጥበብ ቡድን 4ኛ አቃቂ ወረዳ 7 ሳቫኖቫ የኪነጥበብ ቡድን 5ኛ አራዳ ወረዳ 8 ኢትዮ ያሬድ የኪነጥበብ ቡድን በመሆን ለፍፃሜ ውድድር ደርሰዋል
በዘመናዊ ዳንስ 1ኛ ቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 3 አሀዱ የኪነጥበብ ቡድን 2ኛ ለሚኩራ ክ/ከ ወረዳ 13 ጊዮን የኪነ ጥበብ ቡድን 3ኛ ልደታ ክ/ከ ወረዳ 9ቁ1 ሀሌታ የኪነጥበብ ቡድን 4ኛ አዲስ ከተማ ወረዳ 5 ሜዝ የኪነጥበብ ቡድን 5ኛአቃቂ ወረዳ 8 ሰላምና ፍቅር የኪነጥበብ ቡድን በመሆን ለፍፃሜ ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል
የወጣቶች ፌስቲቫል የፍፃሜ ውድድር የካቲት አጋማሽ አከባቢ የሚካሄድ ይሆናል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.