በታዳጊ ምዘና ውድድር የተመዘገቡ 14 የወርቅ ሜ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በታዳጊ ምዘና ውድድር የተመዘገቡ 14 የወርቅ ሜዳልያዎችን ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

በታዳጊ ምዘና ውድድር የተመዘገቡ 14 የወርቅ ሜዳልያዎችን ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

ጥር 30 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

8ኛው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ላይ እየተሳተፋ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ስፓርት ልዑክ ያስመዘገባቸውን የወርቅ ሜዳልያ ቁጥር ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተስራ እንደሚገኝ ተገለጸ

አርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የውሃ ዋና ውድድር የአዲስ አበባ ስፓርት ልዑክ 9 የወርቅ ሜዳልያ መሰብሰቡ መቻሉ ተገልጽዋል

ዛሬ በወላይታ ሶዶ ስቴድየም በተካሄደው የፓራሉምፒክ የፍጻሜ ውድድር 4ወርቅ፣3ብር እና 3ነሐስ በማምጣት መቻሉ ተገልጽዋል

በተያያዘ ዜና ዛሬ በመስማት በተሳናቸው ስፓርት በተደረጉ የፍፃሜ ውድድሮች

1 ወርቅ 1 ብር 3 ነሀስ ሜዳልያዎች መመዝገቡ ተመልክቷል

እስከዛሬው ዕለት የተመዘገበው ውጤት አስደሳች እና ለቀሪ ውድድሮች መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ስፓርተኞች መልካም ውጤት ለማስመዝገብ ያደረጉትን ልምምድ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል

ስፓርተኞች ከተማ አስተዳደሩ የጣለባቸውን ትልቅ አደራ ለመወጣት እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ያወሱት አቶ ጎሳዬ አሰልጣኞች ተወዳዳሪዎች እና ቡድን መሪዎች በቅንጅት በመስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል

ነገ በሚደረጉ የፍጻሜ ውድድሮች ሁሉንም ወርቅ በማምጣት የከተማ አስተዳደሩን ስም ከፍ ለማድረግ ውድድር የሌለባቸው ስፓርተኞች በስፍራው በመገኘት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.