ለ15 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የፖሊስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ለ15 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ለ15 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

የካቲት 01 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ከጥር 17 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርት ውድድር እና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለ15 ቀናት በተካሄደው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር ከተማ አስተዳደሩን ወክለው ለ17ኛ ጊዜ ለሚካሄደው በሀገር አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር የሚሳተፉ ስፖርተኞች በየስፖርት አይነቱ መምረጥ መቻሉን ተናግረዋል።

ስፖርታዊ ውድድሮች በፖሊስ ተቋማት መስፋፋቱ ከውድድር ባለፈ በአባሉ ዘንድ አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን በማጠናከር ጠንካራ የፖሊስ መዋቅር ለመፍጠር እንደሚረዳ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው በሀገራችን የስፖርት ታሪክ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አለማ በአለም አቀፍ የውድድር መድረክ ከፍ ብሎ እንዲወለበለብ ካደረጉ ስፖርተኞች መካከል በርካታዎቹ የወጡት ከፖሊስ መዋቅር ነው ብለዋል።

ለረጅም አመታት ተቋርጦ የቆየው እና በዚህ አመት የተጀመረው ከተማ አቀፍ ፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር በቀጣይም አመታትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል አቶ ዳዊት።

ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል በ5 የስፖርት አይነት በተካሄደው ከተማ አቀፍ የፖሊስ ውድድር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በ9 ወርቅ በ6ብር እና በ4 ነሐስ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ውድድርሩን አጠናቆል።

ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ4 ወርቅ በ4 ብር እና በ5 ነሐስ ሁለተኛ ሲያጠናቅቅ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ3ወርቅ በ2ብር እና በ4 ነሐስ ሜዳልያ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቆል።

በየውድድር አይነቱ አሸናፊ ለሆኑ አካላት የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተበርክቷላቸዋል።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ በተካሄድ የእግር ኳስ የፍፃሜ ጨዋታ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የካ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 ሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮና መሆን ችሏል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.