አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ8ኛው ሀገር አቀ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ምዘና ውድድርን 2ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ/ አቶ በላይ ደጀን

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ምዘና ውድድርን 2ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ/ አቶ በላይ ደጀን

የካቲት 4 ቀን 2017 ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

8ኛው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር በአስር ስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የአዲስ አበባ ከተማ ስፓርት ልዑክ 2ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገለጹ

ስፖርት ልዑኩ 12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በተሳተፉበት ውድድሮች 55 ወርቅ፣52 የብር እና 32 የነሐስ ሜዳልያዎችን ማስመዝገቡ አመርቂ ውጤት ነው ያሉት አቶ በላይ ታዳጊዎችን በጥራትና በስፋት ለማፍራት የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የስፓርት ልዑኩ ቡድኑ ዉጤት አዲስ አበባ በታሪኳ ከፍተኛ የወርቅ ሜዳልያ እንድታስመዘግብ ያስቻለ ነው ያሉት አቶ በላይ በውድድሩ ብዙ ተስፋ የሚጣልባቸው ተተኪ ስፓርተኞችን ያየንበት ነው ብልዋል።

ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ከመጡ ተሳተታፊዎች ጋር ፍፁም ወንድማማችነት እና እህትማማችነት የነበራቸውን ቆይታ ያደነቁት አቶ በላይ በውድድሩ የተገኙ ልምዶችን በመቀመር ለስፓርቱ ሁለንተናዊ እድገት በትኩረት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል ።

ሁሉም የስፓርት አይነቶች የታየውን ከፍተኛ መነቃቃት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ በላይ በፓራሊምፒክና መስማት የተሳናቸው ውድድርን የተገኙ ውጤቶች ለከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል።

የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ አገር" በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከጥር 27 እስከ የካቲት 5 2017ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ስፖርት ምዘና ውድድር ኦሮሚያ ክልል 1ኛ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2ኛ አማራ ክልል 3ኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸው ተመልክቷል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.