በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ልዑካን ቡድን 2.6 ሚልዮን ብር ሽልማት ተበረከተለት።

በ8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ልዑካን ቡድን 2.6 ሚልዮን ብር ሽልማት ተበረከተለት።

የካቲት 08 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በደቡቡ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው 8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ምዘና ውድድር 2ኛ ደረጃ ውድድር ይዞ ላጠናቀቀው ለአዲስ አበባ የስፖርት ልዑክ ቡድን ደማቅ አቀባባበል እና ሽልማት ተበረከተለት።

ለስፖርት ልዑክ ቡድኑ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2.6 ሚልዮን ብር ሽልማት ተበርክቷለታል።

በእውቅናና ሽልማቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ከተማ አስተዳደሩ በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና በሰጠው ልዩ ትኩረት የከተማውን ብሎም የሀገርን ስም እና ሰንደቅ አላማ ከፍ የሚያደርጉ ተተኪ ስፖርተኞች በብዛት እያፈራ ይገኛል ብለዋል።

ከ6 አመት በሆላ በተካሄደውም ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች የምዘና ውድድር 55 ወርቅ 52 ብር እና 32 የነሐስ ሜዳልያ በመሰብሰብ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር በአጠቃላይ139 ሜዳልያዎችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሰብሰብ መቻሉንን አቶ በላይ አሳውቀዋል ።

በውድድሩ ውጤት ያመጡ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ስም ያስጠሩ ስፖርተኞችን፣ አሰልጣኞችን፣ ብድን መሪዎችን እና የስፖርት ባለሙያዎችን አቶ በላይ በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ በሰራባቸው የስፖርት አይነቶች ጥሩ ውጤት መመዝገቡን ተናግረው ውጤት ባላመጣንባችው የስፖርት አይነቶች በቀጣይ በትኩረት አድርገን እንሰራለን ብለዋል።

ከጥር 27 እስከ የካቲት 05/2017ዓ.ም የተካሄደው 8ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች የምዘና ውድድር ፖራ ኦሎምፒክ እና መስማት የተሳናቸው የስፖርት አይነቶችን ጨምሮ በ12 የስፖርት አይነት የተካሄደ ሲሆን ኦሮሜያ ክልል1ኛ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2ኛ እና የአማራ ክልል 3ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.