
አቶ በላይ ደጀን የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ኮንፍረንስ ላይ እውቅና ተሰጣቸው
አቶ በላይ ደጀን የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ኮንፍረንስ ላይ እውቅና ተሰጣቸው
የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የፓን አፍሪካኒዝም አዲስ መንፈስ በግሎባላይዜሽን፣በኢኖቬሽን መር የኢኮኖሚ ውህደት ለሰላም ግንባታ በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ ላይ ለአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጣቸው
በኮንፈረንሱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጨምሮ የፌደራል እና የከተማ አስተዳሩ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ዲፕሎማቶች እና የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት፣ ዩኒቨርስቲዎችና ከሲቪክ ማህበራት የተውጣጡ ከ300 በላይ ወጣት መሪዎች ተሳትፈዋል
የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተሰናዳው ዝግጅት ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ስፓርትን ለዘላቂ ሰላም ግንባታ በመጠቀም ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና ተችሯቸዋል
ያለ ሰላም ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባትና ዘላቂ ዕድገትን ማረጋገጥ አዳጋች ነው ያሉትየቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝን ወጣቶች ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምድ ሊያዳብሩ እንደሚገባ አመላክተዋል
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው በትክክልም አፍሪካን የምንወዳት ከሆነ አንድነቷ ለማረጋገጥ ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም አህጉሪቷን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ሊያውሉ ይገባል ብለዋል።
የአፍሪካ ታላላቅ መሪዎች ለዓለም የነበራቸውን አበርክቶ በንግግሩ ያወሳው የኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር ዳይሬክተር ኢንጂነር ጫላ ኮንፈረንሱ ወጣት አመራሮች ስለዲፕሎማሲ እና ስለ ዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚመክሩበት እንደሆነ ገልጸዋል
በኮንፍረንሱ ላይ የፓንአፍሪካኒዝም እሳቤ አቀንቃኙ ፕሮፌሰር ፓትሪስ ሉሙቧ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ (ዶ/ር) አቶ ቀጀላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የአፍሪካ ወጣቶች ድምጽ ለማሰማት ፍላጎታቸውን ለማሳካት በአንድነት መንፈስ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.