129ኛው የአድዋ ድል ላይ ምክንያት በማድረግ ከ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

129ኛው የአድዋ ድል ላይ ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የፓናል ውይይት ተካሄደ

129ኛው የአድዋ ድል ላይ ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የፓናል ውይይት ተካሄደ

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ 129ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር ከተማ አቀፍ የፓናል ውይይት በአድዋ ድል መታሰቢያ በአድዋ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ

አድዋ የአገር ፍቅር ስሜትና ብሔራዊ ኩራት ጎልቶ የታየበት የአሸናፊነት ሥነ ልቦና ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልድሃና አዲሱ ትውልድ ታሪክ በማዉቅ ታሪክን በማሻገርና ታሪክ በመስራት የልማት አርበኛ መሆን መስራት አለበት ብለዋል ።

አገር መኖሪያም መክበሪያ በመሆኗ ኢትዮጵያዊነት በትልቁ በመገንባት አንድነታችን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ መክብብ የልማት አርበኛ በመሆን የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ወጣቶች በአንድነት መንፈስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል

የዓድዋ ድልና የዘመናችን ትውልድ በሚል ርዕስ ለፓናል የተዘጋጀውን ጽሑፍ ያቀረቡት ዶክተር ተፈሪ መኮንን ከአድዋ የዘመናችን ወጣት ምን ይማራል? አርበኝነት እና የአገር ፍቅር ስሜት? የዲፕሎማሲ ትግልና የተከፈለው መስዋዕትነት በሚሉ ርዕሶች ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል

ድሉ የጎላ ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ ከመስጠቱ ባሻገር የአንድነት እና የትብብር ኃይል ነው ያሉት ዶክተር ተፈሪ ወጣቱ ትውልድ የዓድዋ ድልን ሃውልት በልቡ ውስጥ በመገንባት በአገራችን የተጀመሩ የልማት ስራዎች ላይ ተሳትፎውን ማጠንከር አለበት ብለዋል

የካቲት የጀግንነት የመስዋዕትነት እና የድል ወር መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ አባል ሻምበል ዋኘው ለአገራችን ትልቅ መስዋእትነት የከፈሉ ባለውለታ ጀግኖች አባቶችን አርአያ በማድረግ

ወጣቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ ለመስራት በጋራ መቆም አለበት አሳስበዋል

የውይይቱ ተሳታፊዎች ዓድዋን በመዘከር ለኢትዮጵያን አንድነት በጋራ እንደሚሰሩ በአስተያየታቸው አረጋግጠው በዘመኑ የተሰሩ የልማት ውጤቶችን በመጠበቅ የራሳችን ታሪክ በመስራት የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል

አቶ መክብብ በማጠቃለያ ንግግራቸው በአንድነት መንፈስ የወጣቱን ትውልድ የሚሹ የአርበኝነት ስራ በመሳተፍ የወል የሆኑ ትርክቶችን ይዘን ኢትዮጵያ ከፍ በማድረግ ጠንክረን በመስራት ለዉጣቱ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ እንሰራለን ብለዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.