የአደዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ከ80ሺህ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአደዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ከ80ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።

የአደዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ከ80ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።

የካቲት 22 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

129ኛውን የአደዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ከ80ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአደዋ ድል መታሰቢያ ተካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን አደዋ የአገር ፍቅር ስሜት መገለጫ ብሔራዊ ኩራት እና አሸናፊነት ስነ ልቦና የገነባንበት ነው ብለዋል።

ወጣቶች በአደዋ መንፈስ አርበኝነትን የሚጠይቁ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በመስራት የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ ልትረባረቡ ይገባል ብለዋል አቶ በላይ።

የአሁኑ ትውልድ ለመጪው ትውልድ የአባቶችን ታሪክ ጠብቆ በማሻገር ትላንትን በማክበር፣ ዛሬን በመኖር፣ ነገን በመስራት አገር ወዳድነቱን ማስመስከር አለበት ሲሉ የቢሮው ሀላፊ ተናግረዋል

የዓድዋን ድል በዓል በየአመቱ ስንዘክር ኢትዮጵያዊ አንድነትን አጽንተን በመያዝ የተከፈለውን መሰዋዕትነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት በማዋል ሊሆን እንደሚገባ አቶ በላይ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።

የመቻል ስፓርት ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ኑሩ ሙዘየን በበኩላቸው አድዋ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው የጥቁር ሕዝባች ኩራት መሆኑን ገልጸው

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ ከመፈጸም ባሻገር አባቶቻችን የሰሩትን ድል በልማቱና በስፓርቱ እየደገሙ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

129ኛው የአደዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.