19ኛው ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ፖሊስ ስፖ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

19ኛው ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ፖሊስ ስፖርት ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተጀመረ።

19ኛው ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ፖሊስ ስፖርት ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተጀመረ።

የካቲት 22 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

19ኛው ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ፖሊስ ስፖርት ውድድር ዛሬ በአበበ በቂላ ስታድየም በተካሄደ ደማቅ የመክፈቻ ፕርግራም ተጀምሯል።

በውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ 2ቱ ከተማ አስተዳደሮች እና 12ቱ ክልሎች የሚሳተፉበት ሲሆን በ10 የስፖርት አይነት ለተከታታይ 10 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ክብርት ወይዘሮ ሸዊት ሻንቃ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፤ አቶ መኪዩ ሞሐመድ የባህልና ስፖርት ሚኒሴቴር ድኤታ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ክቡር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት፣ ደንብ ማስከበርና ሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ታድመውበታል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሸዊት ሻንቃ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለስፖርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልፀው አሁን በተለያዩ ቦታዎች እየተከናወኑ በሚገኙት የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ የስፖርት ማዝወተሪያዎች በስፋት እየተገነቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር ዳግም መጀመሩ እንደ ሀገር ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን የጠቀሱት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክብርት ወይዘሮ ሸዊት ሻንቃ ለውድድሩ ለስኬታማነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ቃል ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ክቡር ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሩ 116ኛው የፖሊስ የምስረታ ክብረ በዓል ዝግጅት አካል መሆኑን ገልፀው ውድድሩ በፖሊስ ዓባላት መካከል መቀራረብን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ አክለው በቀጣይ በአፍሪካ ደረጃ ለሚካሄደው የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር ሀገራቸውን የሚወክሉ ስፖርተኞች የሚመረጡበት መድረክ መሆኑንም ገልፀዋል።

ኦሜድላ ስፖርት ክለብ በተለያየ ስፖርት የሀገራቸውን ስም ያስጠሩ በርካታ ስፖርተኞችን ማፍራት መቻሉን አስታውሰው ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር ከዚህ በኋላ በየዓመቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ጀኔራሉ ተናግረዋል።

በመክፈቻው በተካሄደ የሴቶች 5000 ሜትር ውድድር ሲምቦ አለማየሁ ከኦሮሚያ ፖሊስ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ቤተልሔም አስማረ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጣናቃለች።

በእግር ኳስ ፌዴራል ፖሊስ ሶማሌ ፖሊስን 1 ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፎል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.