
አዲስ አበባ ህብረ ብሔራዊት የሰላም የፍቅር እና የብልፅግና ተምሳሌት መሆኗን ያሳየንበት የመክፈቻ ፕሮግራም ነበር። አቶ በላይ ደጀን
አዲስ አበባ ህብረ ብሔራዊት የሰላም የፍቅር እና የብልፅግና ተምሳሌት መሆኗን ያሳየንበት የመክፈቻ ፕሮግራም ነበር። አቶ በላይ ደጀን
የካቲት 23 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር ትላንት በአበበ ቢቂላ ስታድየም በተካሄደ ደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀምሯል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ 2ቱ ከተማ አስተዳደሮች እና 12 ክልሎች የፖሊስ የፖሊስ ስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት የመጡበትን አከባቢ ባህል፣ ታሪክ እና ስልጣኔ የሚያሳዩ የተለያዩ ትርኢቶችን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ህብረ ብሔራዊት፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ መሆኗን ያሳዩበት የመክፈቻ ፕሮግራም እንደበረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ሁሉም ብሔረሰቦች የሚኖሩባት ከተማ መሆኗን የስፖርት ልዑካን ቡድን አባላቱ የሁሉንም ክልሎች ባህል የሚያሳዩ ትርኢቶችን አቅርበዋል።
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች መቀመጫ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ መሆኗን የሚያሳዩ እንዲሁም 129ኛውን የአድዋ ድል በዓል የሚዘክሩ ትዕይንቶች በመክፈቻ ፕሮግራሙ ቀርበዋል።
19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ስፖርታዊ ውድድር እግር ኳስ፣ አትሌትክስ የስፖርት አይነቶችን ጨምሮ በ10 የስፖርት አይነቶች መጋቢት 02/2017ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.