
ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የሳፋሪኮም 5ኪሎ ሜትር የሴቶች የሩጫ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የሳፋሪኮም 5ኪሎ ሜትር የሴቶች የሩጫ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
የካቲት 27 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ማርች 8 የአለም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የሳፋሪኮም 5ኪሎ ሜትር የሴቶች ሩጫ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በእቴጌ መነን አዳሪ የልጅ አገረዶች ትምህርት ቤት ተካሄደ።
ሁሉም መብቶች ለሁሉም ሴቶች በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 5ኪሎ ሜትር የሴቶች የሩጫ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዳ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ዋና ስራ አስኪያጅ ሸለቃ ሀይሌ ገብረስላሴን ጨመም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሴት ተማሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል።
በሩጫው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ዳ/ር ዘላለም ሙላቱ በከተማው በሚገኙ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዘወትር የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚካሄድ ገልፀው በአካል እና በአእምሮ የዳበረ ውጤታማ ትውልድ መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።
ስፖርት ከውድድር በላፈ በተማሪዎች መካከል የእርስ በእርስ ትስስርን በመፍጠር አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን እንደሚያጠናክር ዳ/ር ዘላለም ሙላቱ ገልፀዋል።
ሴቶች መብታቸው ከተጠቀላቸው እና እድል ከተሰጣቸው ማንኛውንም ስራ በተሻለ ደረጃ የመስራት ሀቅም እንዳላቸው የገለፁት የቢሮ ሀላፊው በትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል ከትምህርት ቢሮ ጋር በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት በጋራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የማርች 8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ የሚያዘጋጀዎ 5ኪሎ ሜትር የሴቶች ሩጫ የሴቶችን የስፖርት ተሳታፊነት የሚያሳድግ እና በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የኢትዮጵያን ስም እና ሰንደቅ አላማ ከፍ ያደረጉ ሴት አትሌቶች የሚታወሱበት ነው ብለዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.