የባህል ስፖርት ውድድር እና ፌስቲቫል ለሚሳተፈው...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የባህል ስፖርት ውድድር እና ፌስቲቫል ለሚሳተፈው የስፓርት ልዑካን ሽኝት ተደረገለት

የባህል ስፖርት ውድድር እና ፌስቲቫል ለሚሳተፈው የስፓርት ልዑካን ሽኝት ተደረገለት

የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ለሚካሄደው 22ኛው የባህል ስፖርት ውድድር እና 18ኛው ስፖርት ፌስቲቫል ለሚሳተፈው የአዲስ አበባ ስፓርት ልዑክ ሽኝት ተደረገለት

የብሔር ብሔረስቦች መኖሪያ የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች ማረፊያ አዲስ አበባ ወክለው የሚወዳደሩ የስፓርት ልዑካን ትልቅ አደራ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን አስገንዝበዋል

በአገር አቀፍ የታዳጊዎች ምዘና ላይ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ያስታወሱት አቶ በላይ የአሸናፊነት ሥነ ልቦና ተላብሳችሁ አዲስ አበባ አንደኛ ማድረግ ይጠበቅባችዋል ብለዋል

ባሕላዊ ስፓርቶች ለዘመናዊ ስፓርቶች መነሻ በመሆናቸው ታሪካዊ እሴቶቻቸውን በመጠበቅ ለተተኪው ትውልድ ማሻገር እንደሚገባ አቶ በላይ ገልጸዋል

በውድድር ከማሸነፍ ባሻገር አዲስ አበባን የሚያስጠራ መልካም ስራ መስራት ከስፓርት ልዑክ እንደሚጠበቅ አቶ በላይ አመላክተዋል

ቢሮው ባህል ስፓርትን ለማሳደግ በታዳጊዎች ላይ በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወሱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዳዊት ትርፋ የባህል ስፓርት ውድድር በስኬት ለማጠናቀቅ ተወዳዳሪዎች ከልምምድ ጀምሮ የተሰራውን ስራ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል

ባህላዊ ስፖርቶች ወንድማማችነትን እህትማማችትን ለማጎልበት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው የገለጹት አቶ ዳዊት ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡትን የአሸናፊነት ጉዞ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል

ከ150 በላይ የአዲስ አበባ ስፓርት ልዑካን ወደ ስፍራው በማቅናት በአስረ አንድ የስፓርት አይነት እንደሚሳተፉ ተመልክቷል

ባህላዊ ውድድርና ፌስቲቫሉ ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለጠንካራ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 7 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተመልክቷል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.