22ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

22ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 18ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በይፋ ተጀመረ።

22ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 18ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በይፋ ተጀመረ።

የካቲት 29 / 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

"ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለጠንካራ ኅብረ ብሔራዊ አንደነታችን!" በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሆሳዕና ከተማ በኤርሳሞ አቢዮ መታሰቢያ ስታዲየም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተጀምሯል።

ከ11 ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የባህል ስፖርት ተወዳዳሪዎች እና የባህል ስፖርት ፌስቲቫል አቅራቢዎች የተዘጋጁበትን ባህላዊ ትርዒትና ልዩ ልዩ መገለጫዎቻቸውን በማቅረብ በክብር እንግዶችና በታዳሚዎች ፊት አልፈዋል

በፌስቲቫሉ ማስጀመሪያ የዕለቱ የክብር እንግዳ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንደሻው ጣሰው፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መክዩ ሙሐመድ፣ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሐመድን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል የመንግስት ስራ ሀላፊዎች እና እንግዶችም ታድመዋል ፕሮግራሙን አስመልክተውም መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ተገኝተው የልዑካን ቡድኑን አበረታተዋል

የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መኖሪያ ፣ የአፍሪካና የፌደራል መቀመጫ አለም አቀፍ ሁነቶችንና ኮንፈረሶች የሚካሄዱባት ቲንሿ ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የተሰጠው የአዲስ አበባ የባህል ስፖርቶች ልዑክ ቡድን በመክፈቻው በልዩ ድመቀትና በከተማዋ አምባሳደርነት ጭምር የሚያሳዩ ገፅታዎችን አቅርቧል ።

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን 22ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 18ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል ውድድሩ "ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለጠንካራ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን" በሚል መሪ ሐሳብ በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከየካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 07 / 2017 ዓ.ም ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ይካሄዳል ።

በውድድሩ ትግል፣ ፈረስ ጉግስ፣ ገበጣና ገናን ጨምሮ በ11 አይነት የባህል ስፖርቶች የሚካሄድ ሲሆን ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 370 የሚጠጉ የስፖርት ልዑካንም ይሳተፋሉ ።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.