ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም እና ክህሎት እንዲ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም እና ክህሎት እንዲያዳብሩ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የላቀ ሚና እየተጫወቱ ነው።/አቶ ሞገስ ባልቻ/

ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም እና ክህሎት እንዲያዳብሩ ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የላቀ ሚና እየተጫወቱ ነው።/አቶ ሞገስ ባልቻ/

7ኛው ከተማ አቀፍ የአማተር ኪነ ጥበብ ክበባት ፌስቲቫል ውድድር ተጠናቀቀ።

በዘመናዊ ዳንስ አሐዱ ዘመናዊ የዳንሰ ቡድን በባህላዊ ውዝዋዜ ሳቫኖቫ የባህል ቡድን አሸናፊ ሆነዋል።

የካቲት 30 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል 7ኛው ከተማ አቀፍ የአማተር ኪነጥበብ ክበባት ፌስቲቫል ውድድር ዛሬ ፍፃሜን ሲያገኝ በዘመናዊ ዳንስ አሐዱ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን በባህላዊ ውዝዋዜ ሳቫኖቫ የባህል ቡድን አሸናፊ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የወጣትነት እድሜ በአግባብ ከጠቀምንበት ለአገራችን በጎ አሻራ የምናሳርፍበት ወሳኝ ሰዓት ነው ያሉት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም እና ክህሎት በማዳበር የነገዋን ኢትዮጵያ ለማበልጸግ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል

ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም እና ክህሎት በማዳበር በልዩ ኅብረት የነገዋን ኢትዮጵያ ለማበልጸግ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ አቶ ሞገስ ጥሪ አቅርበዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን

ወጣቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ማጠናከር የዚህ ውድድር ዋና ዓላማ መሆኑን ገልጽዋል

ወጣቶች ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተደራጅተው ከመስራት ባሻገር በተፈጠረላችቸው ዕድል እየተጠቀሙ ይገኛል ያሉት አቶ በላይ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል

ኪነ ጥበብ የሀገርን ባህል እና እሴት ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ የማይተካ ሚና እንዳለው የገለፁት አቶ በላይ በዘርፋ ተተኪዎችን ለማፍራት ከታሰበ አማተር የኪነ ጥበብ ክበባትን መደገፍ እንደሚገባም አሳውቀዋል።

ለአንድ ሃገር ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት አስተዋጽኦ ካላቸው ዘርፎች መካከል ኪነ ጥበብ አንዱ መሆኑን የገለጹት በአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሹክር ትውልዱን ለማነጽ እና የሃገር ፍቅር ስሜት ለማጎልበት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል

ለአራት ወራት በ114 የኪነጥበብ ክበባት መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ፍፃሜውን ባገኝው የኪነጥበብ ክበባት ፌስቲቫል ውድድር ለፍፃሜ የደረሱ 10 ክበባት የተዘጋጁበትን የኪነጥበብ ስራ ታዳሚያን በማቅረብ አድናቆትን አግኝተዋል

ታዳሚያንን በአዝናናው እና ማራኪ የጥበብ ስራ በታየበት በባህላዊ ውዝዋዜ ውድድር ሳቫኖቫ የባህል ቡድን ከአቃቂ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አንድ ኢትዮጵያ ከኮልፌ ሁለተኛ ኢትዮ ያሬዴዊ ሦስተኛ ሲወጣ ህንደኬ ከቦሌ እና ኢትዮ ወግ ከአዲስ ከተማ አራተኛ እና አምስተኛ ሆነው አጠናቀዋል

በዘመናዊ ዳንስ አሀዱ የኪነ ጥበብ ቡድን ከቂርቆስ ውድድሩን ሲያሸንፍ ሀሌታ ከልደታ 2ኛ ሜዝ ከአዲስ ከተማ 3ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሰላምና ፍቅር ከአቃቂ ጊዮን ከለሚ ኩራ አራተኛ እና አምስተኛ. ሆነው አጠናቀዋል

በውድድሩ በአንደኛነት ላጠናቀቁ ተወዳዳሪ ቡድኖች 200ሺ ብር እና የሙዚቃ መሳሪያ ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን ላጠናቀቁ 150ሺ ብር ላፕቶፕ እና ሞንታርቦ ሶስተኛ ለወጡ 100 ሺ ብር እና ሞንታርቦ እና ላፕቶፕ አራተኛ እና አምስተኛ ለወጡ 80ሺ እና የ60 ሺ ብር ተሸላሚ ሆነዋል

በሽብርቅ በተካሄደው ምዘና ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ለሚ ኩራ እና ልደታ ክፍለ ከተማ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ ተቀብለዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.