ክበባት ባህልና ወጋችን ከማስተዋወቅ ባሻገር የአ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ክበባት ባህልና ወጋችን ከማስተዋወቅ ባሻገር የአገራችን የእድገትና የብልጽግና ጉዞ እንደ ዓይናቸው ብሌን የመጠበቅ አደራ አለባቸው /አቶ በላይ ደጀን/

ክበባት ባህልና ወጋችን ከማስተዋወቅ ባሻገር የአገራችን የእድገትና የብልጽግና ጉዞ እንደ ዓይናቸው ብሌን የመጠበቅ አደራ አለባቸው /አቶ በላይ ደጀን/

የካቲት 30 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

7ኛው ከተማ አቀፍ የአማተር ኪነጥበብ ክበባት ፌስቲቫል ውድድር ዛሬ ፍፃሜን ሲያገኝ በዘመናዊ ዳንስ አሐዱ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን በባህላዊ ውዝዋዜ ሳቫኖቫ የባህል ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ትውልዱን የማነጽ እና ወጣቶች አዳዲስ ሐሳቦችን የመፍጠርና የመቀበል እምቅ አቅማቸው እንዲያጎለብቱ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን

የኪነ ጥበብ ስራዎች የሀገርን ባህል እና እሴት ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል

አዲስ አበባ የጀመረችው የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የመሆን ጉዞ እውን ለማድረግ የወጣቶች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አቶ በላይ ገልጸዋል

ቢሮው ኪነ ጥበብ ለአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት የሚሰጠውን ከፍተኛ አስተወጽኦ እንደሚገነዘብ ያወሱት አቶ በላይ ወጣቶች የውድድር ዕድል በማመቻቸት በማበረታት የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል

የከተማችን እንቁ እና የልማት አርበኛ የሆኑ ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ሁለንተናዊ ስፖርት እድገት ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን የገለጹት አቶ በላይ በወጣት ሰብዕና መገንቢያ ማዕከሎች በሚሰጠው አገልግሎት ወጣቱ ዓለምን እንዲረዳ እና አንባቢ እንዲሆን የተደረገው ጥረት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል

ታዳሚያንን በአዝናናው እና ማራኪ የጥበብ ስራ በታየበት በባህላዊ ውዝዋዜ ውድድር ሳቫኖቫ የባህል ቡድን ከአቃቂ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አንድ ኢትዮጵያ ከኮልፌ ሁለተኛ ኢትዮ ያሬዴዊ ሦስተኛ ሲወጣ ህንደኬ ከቦሌ እና ኢትዮ ወግ ከአዲስ ከተማ አራተኛ እና አምስተኛ ሆነው አጠናቀዋል

በዘመናዊ ዳንስ አሀዱ የኪነ ጥበብ ቡድን ከቂርቆስ ውድድሩን ሲያሸንፍ ሀሌታ ከልደታ 2ኛ ሜዝ ከአዲስ ከተማ 3ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሰላምና ፍቅር ከአቃቂ ጊዮን ከለሚ ኩራ አራተኛ እና አምስተኛ. ሆነው አጠናቀዋል

ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ለአራት ወራት በ114 የኪነጥበብ ክበባት መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የተካሄደውን የፍፃሜ ውድድር ለአሸነፉ ክበባት ዳጎስ ያለ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.