
10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና ተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር ነገ መጋቢት 13 ይጀምራል
10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና ተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር ነገ መጋቢት 13 ይጀምራል
መጋቢት 12 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና ተማሪዎች ስፓርታዊ ሊግ ውድድር ነገ መጋቢት 13/2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ስቴድየም በደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ይጀምራል።
ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች ውድድሩን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ውድድሩ የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ፣ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 13 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 4/2017ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልፀዋል።
በውድድሩ 11ዱም ክፍለ ከተማች እንደሚሳተፋ የገለፁት አቶ በላይ እግር ኳስ እና አትሌቲክስን ጨምሮ በ10 የስፖርት አይነቶች በሁለቱም ፃታ ከ26 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በውድድሩ እንደሚሳተፉ አሳውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዳ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች መዘጋጀታቸው የመምህራን እና የተመሪዎችን የእርስ በእርስ ግንኙነትን በማጠናከር በአካል እና በአእምሮ የዳበረ ጤናማ ንቁ እና ብቁ ትውልድን ለመፍጠር ይረዳል ብለዋል።
ትምህርት ቤቶች የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ ተቋማት ናቸው ያሉት ዳ/ር ዘላለም ስፖርትን በትምህርት ቤቶች ባህል ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
ለከተማዋ ሁለተናዊ የስፖርት እድገት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተመላክቷል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.