10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና ተማሪዎች ስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና ተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር ተጀመረ

10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና ተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር ተጀመረ

መጋቢት 13 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ ያዘጋጁት 10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም በተካሄደ ደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተጀምሯል።

የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ፣ ንቁና ቡቁ ትውልድ እንፈጥራለን በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በስፋት ተሳትፈውበታል።

በመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ስፖርት እርቀት ፣ ዘር፣ ሀይማኖት ፣ ቀለም እና ማንንነት ሳይገድበው በሰዎች ዘንድ የእርስ በእርስ ግንኙትን የማጠናከር ሀይል ያለው በመሆኑ ለሀገር ግንባታ ልንጠቅምበት ይገባል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ስፖርትን ለማስፋፋት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከ1ሺህ 3መቶ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን የገለፁት አቶ ሞገስ ጤናማ፣ አምራች፣ ብቁ እና ንቁ ዜጋን ለማፍራት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በሁሉም ቦታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች መካሄዳቸው በመምህራን እና በተማሪዎች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት ይረዳል ብለዋል።

በ10ኛው የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ 11ዱም ክፍለ ከተሞች እግር ኳስን እና አትሌቲክስን ጨምሮ በ10 የስፖርት አይነቶች ውድድሩ እንደሚካሄድ ያሳወቁት አቶ በላይ በአጠቃላይ በሁለቱም ፃታ ከ30ሺህ በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዳ/ር ዘላለም ሙላቱ በአካል እና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ ለማፍራት ስፖርት የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀው በከተማው በሚገኙ ሁሉም ትምህረት ቤቶች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ባህል እየሆነ መምጣቱን አሳውቀዋል።

ለከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገትም የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን ዳ/ር ዘላለም ገልፀዋል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙም በሴት መምህራን የገመድ ጉተታ አቃቂ ቃሊቲ ከ የካ ክፍለ ከተማ ጋር የተካሄደ ሲሆን አቃቂ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ በእግር ኳስ መስከረም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ ደራርቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር ጨዋታቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ።

10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ከዛሬ ከመጋቢት 13 ጀምሮ እስከ የሚያዚያ 04/2017 በከተማው በሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚካሄድ ይሆናል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.