
ቢሮው ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ቢሮው ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
መጋቢት 19 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በከተማው ለሚገኙ የወጣት ስብዕና መገንቢያ መዕከላት ከ30 ሚሊዮን ብር የሚወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አካሄደ።
ቁሳቁሱን ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መክብብ ወልደሀና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በግብዕት የተሞሉ ለማድረግ ቢሮው በየአመቱ የሚያካሂደውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እንደሚገኙ የገለፁት አቶ መክብብ ማዕከላቱን ግብአት ከማሞላት ጀምሮ ለወጣቶች ምቹ፣ ውብ፣ ፅዱና ዘመናዊ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አሳውቀዋል።
ዛሬ ቢሮው ለወጣት ስብዕና ማዕከላት የሙዚቃ መሳሪያ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ጠረፄዛ፣ ወንበር እና የበሀል አልባሳትን ድጋፍ አድርጎል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.