የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ አመት ምክንያት በማድረግ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ከ100 ሺህ በላይ የህብረተሰብ የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።

የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ከ100 ሺህ በላይ የህብረተሰብ የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ።

መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀገራዊ ለውጡን 7ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ከ100 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር አካሄደ።

ትላንት፣ ዛሬ፣ እና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባለፋት 7 የለውጥ አመታት በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እምርታዊ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበት እና በሚሰራበት አከባቢ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋፋታቸው ጤናማ እና አምራች ዜጋን ከመፍጠር ባለፈ የሀገር ስምና ሰንደቅ አላማ በአለም የስፖርት የውድድር መድረክ ከፍ የሚያደርጉ ስፖርተኞችን ለማፍራት ይረዳል ሲሉ አቶ ጃንጥራር ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የቀደሙ አባቶቻችን ሀገራችንን ከውጭ ጠላት ተከላክለውና ልዐላዊነቶን ጠብቀው እንዳስረከቡን ይህ ትውልድም ሀገሩን ከተረጅነት በማላቀቅ እና ኢኮኖሚያዊ ልዓላዊነቶን በማረጋገጥ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለበት ብለዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን መንግስት ለስፖርቱ በሰጠው ልዩ ትኩረት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከ1ሺህ 3መቶ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልፀዋል።

የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በከተማ ደረጃ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ጨምሮ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች እና ፌስቲቫሎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ አቶ በላይ ተናግረዋል።

ዛሬ በአፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር በተካሄደው የብዙሀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም የከተማው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና የከተማው ነዋሪዎች በስፋት ተገኝተዋል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.