ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "አረጋውያንን እመግባለሁ ጤን...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "አረጋውያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ!" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄደ።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "አረጋውያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ!" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄደ።

መጋቢት 28 ቀን 2017ዓ.ም ኸጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ '' አረጋውያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 5ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄደ።

መነሻውንና መድረሻውን አዲሱ ፒኮክ መናፈሻ አከባቢ ባደረገው 5ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ ወጣቶች፣ ታዳጊዎች እና የከተማው ነዎሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል።

ውድድሩን ያስጀመሩት አቶ በላይ ደጀን ህፃናትን እና አረጋውያንን መርዳት እና መከባከብ የአንድ ድርጅት ብቻ የምንሰጠው ሳይሆን የሁላችንም ሀላፊነት በመሆኑ ትኩረት አድርገን ልንሰራበት ይገባል ብለዋል።

ስፖርት ጤንነት ከመጠበቅ ባሻገር የእርስ በእርስ ግንኙነትን በሚያጠናክር አንድነትን፣ አብሮነትን፣ መረዳዳትን፣ ወንድማማችንነትን እና እህትማማችነትን የሚፈጥር በመሆኑ ለበጎ አላማ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ አቶ በላይ ተናግረዋል

የሚሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢዳር ዘውዴ በበኩላቸው ይህ ሩጫ ማህበረሰቡ ለተቸገሩ አረጋውያን ያለውን ድጋፍ ያሳየበት ሲሆን በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ላለፉት 31 ዓመታት ለተቸገሩ ህጻናት እና አረጋውያን የሰብአዊ ድጋፍ ሲያካሂድ መቆየቱን የገለፁት ሲስተር ዘቢዳር በቀጣይም ይህን ድጋፉን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.