
በቢሮው ዘውትር የሰኞ የሚካሄደው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ
በቢሮው ዘውትር የሰኞ የሚካሄደው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ
መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ ዘውትር የሰኞ የሚካሄደው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በስፓርት እና በወጣት ዘርፍ የስራ ክፍሎች ተካሄደ
ዛሬ በተካሄደው የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ላይ የስፓርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉን ጨምሮ የስፖርት ማህበራት ማደራጃና ውድድር ዳይሮክቶሬት፣የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት እና አስተዳደር ዳይሮክቶሬት እና የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት ማስፋፍያና ተሳትፎ ዳይሮክቶሬት እንዲሁም የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል
ለዕለቱ የተዘጋጀውን የእውቀት ሽግግር የማሕበረሰብ አቀፍ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በማህበረሰብ አቀፍ ስፓርት ላይ፣የስፖርት ማህበራት ማደራጃና ውድድር ዳይሮክቶሬት በዘመናዊ የሪፓርት ስርዓት እና በዘመናዊ መረጃ አያያዝ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት አቶ ንብረት ይሁኔ በሞዴል የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት አስራር ላይ ሰፊ ገለጻ ተድርጓል
በእውቀት ሽግግር መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ ስራን ውጤታማ ለማድረግ የዕውቀት ሽግግር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው በመድረኩ የተገኘውን እውቀት በመውሰድ ራስን ለማብቃት እና ለስራ ክፍል ግንባታ ማዋል ይገባል ብለዋል።
የቢሮ ደንበኞች ፍታህዊ አገልግሎት እንዳያገኙና ኢንዲረኩ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ለመዘርጋት እንዲህ አይነት መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዳዊት የጊዜ አጠቃቀማችን በማዘመን የሰፓርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ መስራት ይገባል ብለዋል
የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.