የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖ...

image description
- ውስጥ supporter    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ።

ቢሮው የ2017 በጀት አመት የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ

ሚያዚያ 14 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከሰራተኞች ጋር ገመገመ።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መክብብ ወ/ሀና ባለፋት 9ኝ ወራት በስፖርት ዘርፋም ሆነ በወጣት ዘርፍ በተከናወነ ተግባራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

የወጣቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራውች መሰራታቸውን የገለፁት አቶ መክብብ በከተማ አስተዳደሩ በ9ኝ ወራት የስራ እድል ከተፈጠረላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ከ80 ፐርሰት በላይ ወጣቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበት እና በሚሰራበት አከባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን ባህሉ እያደረገ መምጣቱን ያሳወቁት አቶ መክብብ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን 1400 በላይ ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

የቢሮውን የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ያ አቶ ጌታቸው አበባየሁ የእቅድ በጀት ግምገማ እና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዋል።

በ9ኝ ወራት ከተሰሩ ስራዎች መካከል ከ200ሺህ በላይ ወጣቶች በተፈጠረላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።

በበጎ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ከ21ሺህ በላይ ወጣቶች በ20 የስፖርት አይነት ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ሲሆን በ9ኝ ወራት 257 ኤሊት ስፖርተኞች ማፍራት እንደተቻለ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ከ5.3 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች በሚካሄዱ የብዙን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልፃል።

ለረጅም አመተት ተቋርጠው የቆዩ የፖሊስ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲጀመሩ መደረጋቸው እና ከተማ አቀፍ የባህል፣ የተማሪዎች ፣ የአካል ጉዳተኛ እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድሮች መካሄዳቸው የህብረተሰቡን የስፖርት ተሳትፎ ከፍ ማድረግ እንደተቻል ተመላላክቷል።

በመድረኩ የአራት ኪሎ እና የራስ ሀይሉ ስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.