የታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና...

image description
- ውስጥ supporter    0

የታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና 26 ይካሄዳል።

የታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና 26 ይካሄዳል።

ሚያዚያ 17 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከቅዳሜ ሚዲያና ኢድቨርታይዚግ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት የታዎቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና 26 እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

ሁለቱ ተቋማት ዛሬ በሀርመኒ ሆቴል ፌስቲቫሉን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በፌስቲቫሉ በታዎቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃዊያን እና ቲክቶከሮች መካከል የእግር ኳስ ውድድርን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች እንደሚካሄድ ተገልፆል።

ፌስቲቫሉ በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኝው ቢሪሞ ሜዳ እንደሚካሄድ በጋዜጣዊ መግለጫው የተጠቀሰ ሲሆን ሚያዚያ 23 በጥሎ ማለፍ ውድድር ድምፃዊያን ከ አርቲስቶች እንዲሁም ጋዜጠኞች ከቲክቶከሮች የእግር ኳስ ጨዋታ ሲያካሂዱ የሁለቱ አሸናፊ ቡድኖች ሚያዚያ 26 ለፍፃሜ ጨዋታ እንደሚፋለሙ ተመላክቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መሀሪ ተመስገን የፌስቲቫሉ አላማ በከተማ አስተዳደሩ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የስፖርት ማዘውተሪ ስፍራዎችን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ እንደሆነ ገልፀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከ1300 በላይ ዘመናዊ፣ ምቹ፣ ሳቢና አለምአቀፍ ስታዳርዳቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን የተናገሩት አቶ መሀሪ በነዚህ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅባቸው እንዲሁም ተተኪ ስፖርተኞች በብዛትና በጥራት የሚፈሩባቸው ለማድረግ ቢሮው በተለያዩ ሁነቶቸን በማዘጋጀት እያስተዋወቅ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የቅዳሜ ሚዲያና አድቨርታይዚግ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ አዳነ አረጋ ፌስቲቫሉ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከፌስቲቫሉ የሚሰበሰብ ገንዘብ ለሜቅዶንያ የአረጋውያን እና የአአምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል ይውላል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የቅዳሚ ሚዲያ አድቨርታይዚንግ በከተማዋን የተገነቡ የስፖርት ስፍራዎችን ለማስተዋወቅ የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት አካሂደዋል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.