ባለፋት 9ኝ ወራት ከ200ሺህ በላይ የከተማው ወ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ባለፋት 9ኝ ወራት ከ200ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል

ባለፋት 9ኝ ወራት ከ200ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል። ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ሚያዚያ 18 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ቢሮ የ2017 በጀት አመት የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን ሪፖርትን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።

ቢሮው ባለፋት ዘጠኝ ወራት ለወጣቶች በሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ200ሺህ በላይ ወጣቶች በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሆኑ የአዲስና አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መክብብ ወ/ሀና ተናግረዋል።

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት አና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋን የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቢሮው በበጀት አመቱ 9ኝ ውራት ካቀደው እቅድ አኳያ የተመዘገበው ውጤት አመርቂ መሆኑን አቶ መክብብ ገልፀዋል።

በቀሪ ወራት በበጀት አመቱ ያቀድናቸውን እቅዶች ለማሳካት ጥንካሪዎቻችንን ማስቀጠል ክፍተቶቻችንን መሙላት አለብን ያሉት ም/ቢሮ ሀላፊው ሁሉም አካል ሀላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የቢሮውን የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቶ ጌታቸው አበባየሁ የእቅድ፣ በጀት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዋል።

የወጣቶችን አመለካከት፣ ግንዛቤ እና እውቀት ለማሳደግ ከ2.7ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የማይድ ሴት ፣ የሰራ እድል እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እንደተሰጠ በሪፖርቱ ተመላክቷል ።

ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ከከተማው ወጣቶች ጋር የተለያዩ የፓናል ውይይቶች እና አጫጭር መድረኮች እንዲዘጋጅ መደረጋቸው በዓላቱ ካለምንም የፀጥታ ችግር ማክበር እንደተቻለ በሪፖርቱ ተገልጿል ::

ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በክረምት እና በበጋ ከ84 ሸህ በላይ ታዳጊ ወጣቶች በ19 የስፖርት አይነት በ542 የስጠና ጣቢያዎች ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን 217 አሊት ስፖርተኞችን ማፍራት እንደተቻለ ተመላክቷል ::

ህብረተሰብ በሚኖርበት በሚማርበት እና በሚሰራበት አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን እንደ ከተማ ባህል እየሆነ መምጣቱን በሪፖርቱ የተገለፀ ሲሆን በ9ኝ ወራት ከ 5.3 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ቦታዎች በተዘጋጁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች ተሳታፊ እንደሆኑ ተገልጿል

የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ከማስፋፋት አኳያ ከሀገራዊ ለውጡ ወደህ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከ1400 በላይ ማድረስ እንደተቻለ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

ተቋርጠው የቆዩ የፖሊስ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስፖርታዊ ውድድሮች መጀመራቸው እንዲሁም ከተማ አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች መካሄዳቸው የህብረተሰብን የስፖርት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት አሳድጓል ተብሏል

በመድረኩ የአራዳ እና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤቶች የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ያሏቸውን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን በወረዳዎች የባለሙያ እጥረት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራውች አጠቃቀም እና የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ያጋጠሞቸውን ተግዳሮቶች አንስተዋል።

በተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.