ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ከንቲባ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ማምሻውን የቡልቡላ ፓርክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ማምሻውን የቡልቡላ ፓርክ እና ከቦሌ ኤርፖርት - ካርጎ - ቡልቡላ - አቃቂ ድልድይ ድረስ ያለው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጏል::

ከተማችንን ውብ፣ ጹዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸው ስራዎችን በማጠናቀቅ ከተማችን ፕሮጀክት መጀመር ብቻ ሳይሆን በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደምትችል በማስመስከር ላይ ትገኛለች::

ዛሬ የተመረቀው 21 ሄክታር መሬት የሚሸፍነው የቡልቡላ ፓርክ እና በአጠቃላይ 14 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ከቦሌ ኤርፖርት እስከ አቃቂ ድልድይ ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራ በውስጡ ለህዝብ መገልገያ የሚሆኑ በርካታ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል::

ከነዚህም ውስጥ:-

• የአረንጓዴ ሥፍራና የመንገድ አካፋይ

• ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች

• የቅርጫት ኳስ፣ መረብ ኳስ እና እጅ ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች

• ዘመናዊ የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ስፍራ

• የብስክሌት እና የሩጫ መንገዶች

• የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች

• ፋውንቴኖች እና ፕላዛዎች

• መናፈሻ እና ካፌዎች

• የሕፃናት መጫወቻዎች

• ደረጃቸውን የጠበቁ የመኪና ማቆሚያዎች

• ደረጃውን የጠበቀ ፏፏቴ

• ባሕላዊ ካፌዎች

• ዘመናዊ ካፌዎች

• ጁስ ባር

• አምፊ ቴአትር

• ዘመናዊ የሠርግ እና የሙሽራ ቦታ

• የካምፕፋየር ቦታዎች

• የእግረኛ መንገዶች፣ መብራት እና አደባባዮች

• ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የምግብ መስተንግዶ ቦታዎች

• ከ380 በላይ የሕንፃ እድሳት፣ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ሱቆች እንዲሁም በርካታ መሠረተ ልማቶች የተሟሉለት ደረጃውን የጠበቀ የመዝናኛ እና መናፈሻ ሥፍራ ነው፡፡

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.